እንኳን ደህና መጣችሁ
እንኳን ደህና ወደ አገልግሎቱና ወደ ዙፋኑ ሕይወት ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን በደህና መጣችሁ።
ይህ አገልግሎት በመለኮት ፈቃድና ምሪት ከጌታ በተቀበልነው መልእክት የተጀመረ ሲሆን ሁላችንም በመንፈስ ቅዱስ ለክርስቶስ ቀን (ለንጥቀት) እንድንዘጋጅና ለዙፋኑ ሕይወት ክብር እድንበቃ ጌታ በሰጠን በራሱ ፀጋ የሚሰራብን በመሆኑ፣በጉ (ክርስቶስም) በእኛ ምክንያት እንዳይዘገይ ለማፍጠን የወንጌልን እውነት በሃይልና በመንፈስ ቅዱስ በመግለጥ ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ቤተክርስቲያን ማለት የመሰብሰቢያ አዳራሹ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነን የዳንን ሁላችንም ስለሆንን ኑና አብረን በክርስቶስ ኢየሱስ ስር ሰደው እና ጸንተው ከሚጠብቁ፣ከሚያስቸኩሉና ከሚነጠቁት ከጥቂቶቹ ተርታ ለመሆን አብረን እንሰራ፣ እንዘጋጅ ።ዮሀንስ14:1-3
ቡሩካን ናችሁ።